“የልዩ ኀይል ሪፎርም የተተገበረው በክልል የተከፋፈለ ልዩ ኀይል ሳይኾን ሰብሰብ ያለና ጠንካራ ተልዕኮውን መወጣት የሚችል የጸጥታ ኀይል ለመገንባት ነው” የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኀላፊ

87

ባሕርዳር : ግንቦት 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽንን ተቀላቅለው በመሠልጠን ላይ የሚገኙ የቀድሞ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ሥልጠና ላይ በመገኘት መልእክት አስተላልፊዋል።

የአማራ  ልዩ ኀይል ለአማራ ክልል ብቻ ሳይኾን  ከውስጥም ከውጭም ሀገርን ለማፍረስ የሚታትሩ ጸረ ሰላም ኀይሎችን ያንበረከከ ነዉ ብለዋል። ያንን ታሪክ እና ጀብድ በመፈጸም ድል እንዳደረጋችሁት ሁሉ ዛሬም አንድንነትን መሠረት ያደረገና ህብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊነትን ያነገበ ሠራዊት አቶ ደሳለኝ።

መንግሥት የሚያመጣቸውን የለውጥ ሀሳቦች በመቀበል ለተጨማሪ ተልዕኮ ተዘጋጅታችሁ ሀገርንና ሕዝብን ለማገልገል ዝግጁ በመኾን ጀግነታችሁን በተግባር መድገም አለባችሁ ብለዋል ኀላፊው።

አቶ ደሳለኝ ሠልጣኞቹን የተቋቋማችሁበት  ዋና አላማ ግቡን የመታ ነው ብለዋል። ሪፎርሙ የተተገበረውም በክልል የተከፋፈለ ልዩ ኀይል ሳይኾን  ሰብሰብ ያለና ጠንካራ ተልዕኮውን ለመወጣት የሚያስችል የጸጥታ ኀይል ለመገንባት ታስቦ የተደረገ መኾኑን አቶ ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡

አንዳንድ ሀገር አፍራሾች ይህንን የሀገር ባለውለታ የአማራ ልዩ ኀይል ወዳልተገባ ጥፋት ለማስገባትና  ክልሉን ለማፍረስ የሚያሰራጩትን አሉባልታ ወሬ በመተው  መንግሥት የሰጣቸውን ተልዕኮ በመቀበል ሕዝብንና ሀገርን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸው  አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡

ሠልጣኞቹ የክልሉን ማረሚያ ቤት ፖሊስን በመቀላቀል በሠራው ወንጀል የሚፀፀት  የተሻለ ሥነ ምግባር ያለው ታራሚ ለመፍጠር  መሥራት አለባችሁ ነው ያሉት።  አንድነትን በማጠናከር የአባቶቻችሁን ታሪክ መድገም አለባችሁ ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ማረሚያቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር  ደስየ ደጀኔ  እንዳሉት የክልሉን ማረሚያ ቤት የተቀላቀሉ የቀድሞ ልዩ ኀይል አባላት  በደቡብ ጎንደር ዞን ዓለም በር ማሰልጠኛ ማዕከል ገብተው እየሠለጠኑ መኾኑን ገልጸዋል።

ክልሉን በማንኛውም ነገር ተወዳደሪ ለማድረግ ሰላምን ማስፈን ይገባል፤ የክልሉን  ሰላም ለማረጋገጥም አንድነታችንን በማጠናከር ችግሮችን በንግግር መፍታት ይገባል ብለዋል፡፡

መቶ አለቃ ምህረት ሞላ እና ኮንስታብል አስካል ዓለሙ የክልሉን መንግሥትና ሕዝብ በቅንነትና በታታሪነት ለማገልገል የማረሚያ ቤት ፖሊስ አባል በመኾን ሥልጠና እየወሰዱ መኾኑን ከAPP ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በማሰልጠኛ ማዕከሉ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰውን ጨምሮ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደጀኔ ልመንህ ፣ የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀኔ፣ የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኮሌኔል ባምላኩ ዐባይ ሠልጣኞችን ጎብኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የመካነ-ኢየሱስ/እስቴ-ስማዳ 50 ነጥብ 5 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ወደ መጠናቀቅ ተቃርቧል” የኢትዮጵያ መንገዶች ባልስልጣን
Next articleየአማራ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በሥነ ምግባርና ግብረ ገብነት ግንባታ ዙሪያ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።