“አፈጻጸማችንን በማሻሻል የምናገለግለውን ማኅበረሰብ እርካታ ማሳደግ ይጠበቅብናል” የአማራ ክልል የከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ

46

ባሕር ዳር: ግንቦት 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ ከከተሞች፣ ከከተማ አሥተዳደሮች እና አጋር አካላት ጋር የ2015 በጀት ዓመት የ3ኛው ሩብ ዓመት አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው።

የአማራ ክልል የከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ ቢያዝን እንኳኾነ ግምገማው ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በቀሪ ወራት የሚሠሩ ተግባራትን ለመለየት እንደኾነ ነው የተናገሩት።

ውብ ከተማ ከመኖሪያ ቤት ይጀምራል ያሉት አቶ ቢያዝን ከተሞችን ውብ ለማድረግ እያንዳንዱ የሚጠበቅበትን መሥራት እንዳለበት አስረድተዋል፡፡ ከተማን ውብና ለጎብኝዎች ተመራጭ ለማድረግ መሥራት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል፡፡

አቶ ቢያዝን “አፈጻጸማችንን በማሻሻል የምናገለግለውን ማኅበረሰብ እርካታ ማሳደግ እና የአገልግሎት ጥራቱን ማሻሻል ይጠበቅብናል” ነው ያሉት።

የከተማ ነዋሪዎችን የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ሕዝቡ ኢኮኖሚ እንዲያመነጭ ማድረግ ዋናው ተግባር ሊኾን እንደሚገባም አሳስበዋል።

የሕዝቡን ፍላጎት ለማርካት ኀላፊነትን በአግባቡ መወጣት እንደሚያስፈልግም አቶ ቢያዝን አንስተዋል።

ዘጋቢ :- ትርንጎ ይፍሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሀገር ስትፈልገን ሁሌም ዝግጁ ነን!” የቀድሞ ከፍተኛ የአማራ ልዩ ኀይል መኮንኖች
Next article“ጥሩ ሀገር ለመገንባት ቅድሚያ ጥሩ ቤተሰብ መገንባት ላይ መሥራት ይኖርብናል” የአማራ ክልል ሴቶች ሕጻናትና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ