በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጽንፈኛ ኀይሎችን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

119

ባሕር ዳር: ግንቦት 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሰቆጣ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ መላሽ ወርቃለም በሰላማዊ ስልፉ አማራ ክልልን መሪ አልባ ለማድረግ በሚሠሩ ጽንፈኛ ኀይሎችን በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንዲኾኑ መንግሥት በቁርጠኝነት ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

ፅንፈኞች በክልሉ መሪዎች ላይ እያደረሱ ያሉትን መጠነ ሰፊ ጉዳት አንታገስም ሲሉ ገልጸዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በአካባቢያችን በነበረዉ ጦርነት የደረሰብንን ግፍ እና መከራ የዋግ ኽምራ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል፤ የሰላምን ዋጋም እንዲሁ ያሉት የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ዋና አሥተዳዳሪ ስቡህ ገበያዉ (ዶ.ር) አሁን ላይ የተገኘዉ አንፃራዊ ሰላም በምንም መልኩ ሊቀለበስ አይገባም ነው ያሉት።

በሰላም እጦት ሁላችንም እየታመስን መኖር የለብንም ያሉት ዶክተር ስቡህ የቃየል እና የአቤል አይነት ግድያ በወንድማማቾች መካከል እየተፈጸመ ያለዉ አስነዋሪ ተግባር ሊቆም እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

ሕዝባችን የሰላምን ሁለንተናዊ ምንነት ስለሚረዳ በጦርነቱ ሀብቱን ፣ሕይወቱን እና የሥነ ልቦና ችግር ተጎጂ ሆኖ ያለፈበትን መከራ በእርግብ አምሳል ተመስሎ በሰላማዊ ሰልፍ የጦርነትን አስከፊነት ለመግለጽ አደባባይ መውጣቱ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል ዋና አሥተዳዳሪዉ።

የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ አቶ ሸጋው በሬ እንደተናገሩት የአማራ ክልል መንግሥትና ብሔረሰብ አሥተዳደሩ ፅንፈኛ ኀይሎችን ከገቡበት ገብቶ እንደ መንግሥት ሥርዓት ማስያዝ አለበት ነዉ ያሉት።

የተካሄደዉ ሰልፍም የዋግ ኽምራ ሕዝብ ለፅንፈኛ ኀይሎች የማይንበረከክና ለኢትዮጵያዊ ማንነቱ የማይደራደር መኾኑን ያሳያል ማለታቸውን ከአሥተዳደሩ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

መንግሥት በነዚህ ጽንፈኛ ኀይሎች ላይ እየወሰደ ያለዉ እርምጃ ሰላምን ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና ስላለዉ የዋግ ኽምራ ሕዝብ ስላምን አጥብቆ ስለሚፈልገዉ ከመንግሥት ጎን ሆኖ ፅንፈኞችን ያውግዛል ብለዋል።

በሕዝባዊ ሰልፊ ላይ እኛ የዋግ ኽምራ ነዋሪዎች በህብረ ብሔራዊ አንድነትና በኢትዮጵያዊነት የምናምን እንጅ ለጽንፈኛ ኀይሎች የማንበረከክ መኾናችን እናሳውቃለን፤ የክልላችን ልማት በነውጠኛ ኀይልች አይቀለበሰም

የሚሉና ሌሎች የተለያዩ መልእክቶች ተላልፈዉ ሰልፉ በሰላማዊ መንገድ ተጠናቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ600 በላይ ባለሀብቶች ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር ተጠቃሚ አድገናል” የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት
Next article“በ2015/16 ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ አቅደን እየሠራን ነው፡፡” የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር