“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መስፈን እያከናወነች ያለውን ተግባራት አጠናክራ ትቀጥላለች” ቅዱስ ሲኖዶስ

101

ባሕር ዳር: ግንቦት 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መስፈን እና ለምዕመናን ደኅንነት እያከናወነች ያለውን ተግባራት አጠናክራ እንደምትቀጥል የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ።

ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጉባዔው በተጀመረበት ወቅት እንደገለጹት፣ ቤተክርስቲያኗ ከመንፈሳዊ ተግባራት ጎን ለጎን የሰላም፣ የዕርቅ እና ሌሎች ዕሴቶችን ለምዕመኑ የማስተማር ሥራዎች እያከናወነች ትገኛለች።

ይህንን ተግባሯን በማጠናከር አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የቤተክርስቲያኗ አባቶች ተግተው ሊሠሩ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት እና መግባባት መፍታት ይገባልም ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ በቤተክርስቲያኗ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠቁመዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው የጤና ተቋማት በመልሶ ማቋቋም አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ ተገለጸ።
Next article“ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ600 በላይ ባለሀብቶች ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር ተጠቃሚ አድገናል” የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት