በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በስድስት ወራት 100 ቤቶች ለነዋሪዎች ሊገነቡ ነው፡፡

294

ተቀማጭነቱ አሜሪካ የሆነ ቪሌጅ ሶሊሽን ኩባንያ ከአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ጋር በመተባበር በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ዘመናዊ መንደር መገንባት የሚያስችል የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡

በዘመናዊ መንደር ፕሮጀክቱ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ደረስጌ ማሪያም ቀበሌ 100 ቤቶችን ግንባታ እንደሚያከናውንና የተሟላ የመሠረተ-ልማት ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው የቢሌጅ ሶሊሽን ዓለማቀፍ ፕሪዝዳንት ስቴቭ ጅዋንስ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፋንታ እንደገለፁት ዘመናዊ የመንደር ግንባታ ፕሮጅክቱ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው፤ የአካባቢውን ነዋሪዎች የተሻለ ሕይወት ለመምራትና መሠረተ-ልማት የተሟላበት ኑሮ እንዲኖሩ የሚደረግ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ በቀጣይ ፕሮጀክቱ በክልሉና በሀገሪቱ የተላያዩ አካባቢዎች የማስፋት ሥራ እንደሚካሄድም አቶ መላኩ ገልፀዋል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በሪሁን ካሳው ደግሞ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ 38 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱንና ተጀምሮ እኪጠናቀቅም ከተማ አስተዳደሩመና ነዋሪዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡

በመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ መርሀ ግብሩ የደረስጌ ማሪያም ቀበሌ ነዋሪዎች፣ የቪሌጅ ሶሊሽን የኢትዮጵያና አፍሪካ ዳይሬክተር ፓስተር ጌታሁን ነሲቡ እንዲሁም የአማራ ልማት ማኅበር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

መረጃውን ያደረሰን አልማ ነው፡፡

Previous articleልዩ ልዩ መሣሪያዎችን በመጠቀም ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያትሙ የነበሩ የውጪ ሀገር ዜጎችን በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
Next article‹‹ለኅብረተሰባችን ፈውስ እንጅ ሕመም ላለመሆን እንማራለን፡፡›› የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች