ኢትዮጵያና ዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ ከ106 ሚሊዮን ዶላር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

50

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (አይ ኤፍ ኤ ዲ) ከ106 ሚሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ  የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ክልል ዳይሬክተር ሣራ ምባንጎ-ቡን ተፈራርመዋል፡፡

የድጋፍ ገንዘቡ ከአይ ኤፍ ኤ ዲ 78 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ፣ ከአውሮፓ ኅብረት 17 ነጥብ 84 ሚሊየን ዶላር  እና ከኤ ኤስ ኤ   10 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር  የተሰባሰበ መሆኑ  ተገልጿል፡፡

ከድጋፉ የሚገኘው ገቢ በኢትዮጵያ የአሳታፊ ግብርና እና የአየር ንብረት ለውጥ  ፕሮግራም ትግበራ ይውላል ነው የተባለው።

የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ በተመረጡ የገጠር ቀበሌዎች የ150 ሺህ ቤተሰቦች ገቢን፣ ምግብን እና አመጋገብን በዘላቂነት ማሻሻል እና የአየር ንብረት ለውጦችን የመቋቋም አቅምን መገንባትም እንደሆነ ተመላክቷል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ፕሮግራሙ ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ላይ የሚያተኩር ነው። ድህነትን ለመቀነስ እና የመቋቋም አቅምን ለማሻሻል የተነደፈ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
Next articleስልጣንንና ፍላጎትን በኀይልና በጉልበት ለመጫንና ለመንጠቅ የሚደረግን እንቅስቃሴ መታገል እንደሚገባ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ገለጸ።