
ደሴ: ሚያዝያ 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን በሃርቡ ከተማ አሥተዳደር በኀብረተሰቡ እና በአጋር ድርጅቶች ተሳትፎ በ23 ሚሊዮን ብር የተገነባው ትምህርት ቤት ተመርቋል።
ትምህርት ቤቱ በዋናነት በኀብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባ ሲኾን መንግስት እና አጋር ድርጅቶችም ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።
በምረቃ መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ሁሰን የሃርቡ ተወላጆች ለዚህ ትምህርት ቤት ግንባታ ያከናወኑት ተግባር የሚያኮራ እና የሚያስመሰግን መኾኑን ገልጸዋል።
ትምህርት ለሁሉም ነገር መሰረት በመኾኑ የትምህርት ቤቱ ህንጻ ግንባታ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የከተማዋ ነዋሪዎችና ተወላጆች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ለሌሎችም ምሳሌ የሚኾን ነው ብለዋል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ቢጠናቀቅም በውስጡ ብዙ የሚቀሩት ቁሳቁስ መኖራቸውን የገለጹት ዋና አሥተዳዳሪው፤ ዞኑ ይህንን ለማሟላት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ትምህርት ቤቱ ባለ አራት ወለል ሲኾን 16 የመማሪያ ክፍሎች አሉት።
ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!