ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በፋርማስቲካል ኢንዱስትሪ ዘርፍ ሊሰማሩ መኾኑ ተገለጸ።

92

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከሚገቡና ከ8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ካስመዘገቡ 10 ሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ።

ከእነዚህ ኩባንያዎች ዉስጥ አምስቱ በፋርማስቲካል ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ እንደሚሠሩ ኢፕድ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽኑ የሀገር ዉስጥ ማኒፋክቸሪንግና የግል ዘርፍ እንዲጠናከር እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት ትላልቅ የውጭ  ኩባንያዎች ወደ ሀገር ዉስጥ ገብተዉ እየሠሩ ቢሆንም የሀገር ዉስጥ ኩባንያዎችንም ለማካተት ትኩረት ሰጥቶ እየተሠራ ይገኛል።

በዚህም 10 የሀገር ዉስጥ ኩባንያዎች በኢንደስትሪ ፖርክ ለማልማት ስምምነት ፈጽመዋል። ኩባንያዎቹ ለ7ሺ ዜጎች የሥራ እድል የሚፈጥሩ ናቸው ተብሏል።

ከእነዚህ ኩባንያዎች ዉስጥ አምስቱ በፋርማስቲካል ኢንደስትሪ ዘርፍ የሚሠማሩ ናቸው። በመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ለማስገባት የሚወጣዉን የውጭ ምንዛሬ እንደሚያስቀር አቶ አክሊሉ ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

 

Previous articleየደጀን ወረዳ በወተት ላም እርባታ ዘርፍ የሥራ እድል እና ከፍተኛ ገቢ እያገኘ መኾኑን ገለጸ።
Next articleየደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ከሃያ ሺህ ጫማ ከፍታ በላይ መጓዝ የሚችል ሮኬት አስወነጨፈ።