በአማራ ክልል መሪዎች በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለውን ግድያ እንዲሁም ሰላምን የሚያውኩ ድርጊቶች የሚያወግዝ ሰልፍ በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አሥተዳደሮች ተካሄደ።

944

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል መሪዎች በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለውን ግድያ እንዲሁም ሰላምን የሚያውኩ ድርጊቶች የሚያወግዝ ሰልፍ በደቡብ ወሎ ዞን የተካሄደው።

በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አሥተዳደሮች በዛሬው ዕለት በተካሄደው ሰልፍ የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ኾነዋል። ሃሳብ በሃሳብ እንጅ በጠመንጃ አይገነባም፣ ጠመንጃ ሀገር ያፈርሳል፣ መሪን በመግደል የሚቆም ምንም ዓይነት ትግል የለም፣ መንግሥትን ሕግ የማስከበር ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥል እንፈልጋለን፤ እኛም እናግዛለን!! ብለዋል በመፈክሮቻቸው።

ከደቡብ ወሎ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በሰልፉ ላይ ሃሳብን በዴሞክራሲያዊ ትግል እንጅ አፈ ሙዝ የደካሞች ባህሪ ነው፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዋስትናችን ነው፤ ለክብሩም ደጀን እንኾናለን፣ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጎልበት ለኢትዮጵያ አንድነት እንተጋለን የሚሉ መፈክሮች በሰልፎቹ ተስተጋብተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጀግንነትና አርበኝነት የኢትዮጵያውያን የአባት ውርስ ነው!
Next articleየደጀን ወረዳ በወተት ላም እርባታ ዘርፍ የሥራ እድል እና ከፍተኛ ገቢ እያገኘ መኾኑን ገለጸ።