
ባሕር ዳር:ሚያዝያ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ እና የሀርቡ ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች የአቶ ግርማ የሺጥላን ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ነው። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ መሪን በመግደል የሚቆም ትግል የለም፤ መከላከያ ሰራዊታችን የሀገር መከታ ነው፤ ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችም ተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!