
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ያስገነባውን ቁጥር ሁለት ስካይ ላይት ሆቴል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ዛሬ በይፋ አስመርቋል።
በመረሃ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ዲፕሎማቶች ታድመዋል። ምዕራፍ ሁለት የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በአፍሪካ ደረጃ እጅግ ዘመናዊ መሆኑ በዚሁ ወቅት ተገልጿል። መረጃው የኢዜአ ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!