የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ከድል ሃውልቱ ስር የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ።

50

ሚያዝያ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 82ኛው የኢትዮጵያ ዐርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል በአዲስ አበባ አራት ኪሎ እየተከበረ ነው።በዓሉ አራት ኪሎ በሚገኘው የአርበኞች ድል መታሰቢያ ኃውልት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል ።

“አብሮነት ለጽናትና ድል” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ በሚገኘው የመታሰቢያ በዓል ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ከድል ሃውልቱ ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በመታሰቢያ በዓሉ ላይ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ፣ አባትና እናት አርበኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።በዓሉን ምክንያት በማድረግም ንጋት ላይ መድፍ ተተኩሷል።

አርበኝነት የመላው ኢትዮጵያውያን የነጻነትና የአንድነት መገለጫ በመሆኑ በመስዋዕትነት ሀገርን በአንድነት ላቆዩልን ጀግኖች ዐርበኞቻችን በየዓመቱ ሚያዝያ 27 በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጠላት ተሰበረ፣ ዙፋኑ ከበረ”
Next article“አንዲት ግራር” የሸዋ አናብስት አሻራ!