
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 06/2012 ዓ/ም (አብመድ) በሠላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት የአማራ እና ትግራይ ምሁራን በሠላም ዙሪያ አዲስ አበባ ላይ እየተወያዩ ነው፡፡
በውይይቱም የአማራና ትግራይ ሕዝቦች የአብሮነት እሴት በፖለቲካ ልሂቃን ጥቃቅን ልዩነት ለከፋ ብጥብጥ መዳረግ እንደሌለበት ተመላክቷል፡፡
የፖለቲካ ልሂቃኑ የተሻለ ሐሣብና አጀንዳ በመቅረጽ ለሠላም እንዲሠሩም ተጠይቋል፡፡ ሁለቱን ሕዝቦች በብሔር፣ ጎሳና አካባቢያዊነት መደብ ከመከፋፈል ተወጥቶ አንድነት ላይ እና ችግር ፈች ጉዳዮች ላይ መሥራት የሚያስችሉ ሐሳቦች ላይ ማተኮር እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡
ዘጋቢ፡- ጽዮን አበበ -ከአዲስ አበባ