
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ልዩ መልክተኛ ጋር መወያየታቸውን ገለጹ።
ሱዳን አሁን ከገባችበት ቀውስ በራሷ አቅም እና በልጆቿ ብልሃት የመውጣት ብቃቱ እንዳላት የኢትዮጵያ እምነት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በሀገሪቱ ግጭት ውስጥ የገቡት አካላት ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱም ጥሪ አቅርበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!