
አዲስ አበባ: ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የአሥተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ የሳይበር ጥቃት ኢላማ ከተደረጉ ተቋማት መካከል ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት፣ የጸጥታና ደኀንነት ፣ የሚዲያና ሌሎች የመንግሥት ቁልፍ ተቋማት ይገኙበታል ብለዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደኀንነት አሥተዳደር የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኀንነት አሥተዳደር ባለፉት 9 ወራት የሳይበር ጥቃቶችን በመከላከል 19 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉ ተገልጿል። በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በሀገራችን 4 ሺህ 422 የሳይበር ጥቃቶችን እና የጥቃት ሙከራዎች የተፈጸሙ መኾኑን ገልጿል። ከእነዚህ መካከል 4 ሺህ 272 ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ በሂደት ላይ መኾናቸውን ነው ዋና ዳይሬክተሩ ሰለሞን የተናገሩት። ጥቃቶቹ ቢደርሱ ኖሮ የመሠረተ ልማቶች መቋረጥ፣ ተቋማት የሚሰጧቸው አገልግሎቶች መስተጓጎልና የገቢ መስተጓጎል ይደርስ ነበር ተብሏል።
ዘጋቢ፡- ድልነሳ መንግሥቴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!