የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

128

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል። ኦላፍ ሾልዝ አዲስ አበባ ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያና አቀባበል አድርገውላቸዋል።

መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በሁለትዮሽ፣ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበበልግ ዝናብ ከተሸፈነው መሬት 7 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል እንደሚጠበቅ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
Next articleየኢንፎርሜሽን መረብ ደኀንነት አሥተዳደር ባለፉት 9 ወራት የሳይበር ጥቃት ሙከራን የመመከት አቅሙ 94 ነጥብ 8 ከመቶ መድረሱን አስታወቀ፡፡