
ባሕር ዳር:ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኃይለማርያም ከፍያለው (ዶ.ር) ዛሬ በሰጡት መግለጫ በ5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 160 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል።
ከባለፈው ዓመት የምርት ዘመን ጋር ሲነጻጸር 20 ሚሊዮን ኩንታል ጭማሪ ያለው ዕቅድ መኾኑንም ተናግረዋል።
ዕቅዱ ሰፊ የኾነው ካለው አቅም አንፃር መኾኑንም ገልጸዋል። የአማራ ክልል ታላቅ አቅም ያለው ክልል ነው ያሉት ኃላፊው በግብርናው ዘርፍ በትኩረት ከተሠራ ክልሉም፣ ሀገሪቱም ተጠቃሚ ይኾናሉ ነው ያሉት።
አጠቃላይ ከታቀደው 160 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል፦
➨ከምግብ ሰብል 95 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል
➨ከኢንዱስትሪ ሰብል 53 ሚሊዮን ኩንታል
➨ለውጭ ገበያ ከሚቀርቡ ምርቶች 12 ሚሊዮን ኩንታል ይጠበቃልም ብለዋል።
በክልሉ ሰንዴ፣ ጤፍ፣ ማሽላ፣ በቆሎ፣ አኩሪ አተር፣ ሩዝ፣ ሰሊጥ በስፋት እንደሚመረቱም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!