
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሠላማዊ የመማር ማስተማር እና መልካም አስተዳድርን ለማስፈን እየተሠሩ ባሉ ሥራዎች ዙሪያ ነው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሪዎች እየተወያዩ ነው፡፡
ሁሉንም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነባራዊ ሁኔታ ማዕከል ባደረገ መልኩ የለውጥ ሥራ አመራር፣ የመልካም አስተዳደር የአሠራር እና የአደረጃጀት መመሪያ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማዘጋጀቱን ነው በጉባኤው የገለፁት።
መመሪያው በመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሠላማዊ የመማር ማስተማር፣ የምርምር እና የማኅበርሰብ አገልግሎት ተልዕኮዎችን በላቀ ሁኔታ መፈፀም የሚያስችል መሆኑም ተመላክቷል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ የትህምርት ተቋማት ሠላማዊ የመማር መስተማር እና የመልካም አስተዳድር ሥራዎች ስኬታማነት ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡
በውይይቱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና ከ45 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።