ተመድ የሰላም ስምምነት ትግበራውን እንደሚደግፍ አስታወቀ።

102

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግባራን በሁሉም መስክ እንደሚደግፍ አስታውቋል።

የድርጅቱ ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ዛሬ ጽ/ቤታቸው ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ መፍታቷን አድንቀው ፈታኝ የሆነውን የሰላም ሂደት ትግበራ በሁሉም መስክ እንደግፋለን ብለዋል። በኢትዮጵያ የመልሶ ማቋቋም ዳግም ግንባታ እቅዱን ማገዝ እንደሚገባ ጠቅሰው ሰላሙ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው፣ የሰላም ሂደቱን በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው የሰላም አጀንዳው በሌሎች አካባቢዎች ለመፈፀም መንግሥት እየሠራ ነው ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም ይህን ጥረት የሚመጥን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅበትም አቶ ደመቀ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ለሚዛን አማን ከተማ አሥተዳደር የ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
Next articleኢትዮጵያ ስድስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።