ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር አካል የኾነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፈቱ::

142

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር አካል የሆነውን ሐላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው ከፍተዋል።

በምርቃቱ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የክልል ርእሳነ-መሥተዳድሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ሪዞርቱ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ መጠናቀቁ ተገልጿል። የፕሮጀክቱ ግንባታም የአካባቢው ማኅበረሰብ ነባር የኪነ-ሕንጻ ጥበብን ከዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ጋር በማናበብ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ተገልጿል። በውስጡም ፕሬዝዳንታዊ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ዘመናዊ መኝታ ክፍሎች እና ሌሎች የመዝናኛ ስፍራዎችን የያዘ ነው።

ሪዞርቱ በተገነባበት ስፍራ የሚገኘው የጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ሰው ሠራሽ ሐይቅም በውሃ ላይ መዝናናት ለሚፈልጉ ጎብኝዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ሆኖ መዘጋጀቱን ኢዜአ ዘግቧል።

በተጨማሪም ቀደምት የዳውሮ ንጉስ ሃላላ የተገነባው የሃላላ ድንጋይ ካብ (ሃላላ ኬላ) ታሪካዊነቱን እንደጠበቀ በስፍራው ተጨማሪ የመስህብ አካል በመሆን ያገለግላል። የሪዞርቱ መገንባትም ለአካባቢው ማኅበረሰብ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ6 ሺህ በላይ የሱዳን ተፈናቃዮች በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ገለጸ።
Next article“ሜይ ዴይ” ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን ጥቅምና መብትን በትግል የማጽናት ተምሳሌት!