በቀን 288 ሺህ እንጀራ የሚጋገርበት ማዕከል ተመረቀ።

115

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ በቀን 288 ሺህ እንጀራ የሚጋገርበትና እንጀራን ኢንዱስትራላይዝ በማድረግ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው ለሚ እንጀራ ማዕከል መመረቁ ተገለጸ፡፡

ማዕከሉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች ጋር በመሆን መርቀዋል፡፡

ለሚ እንጀራ ማዕከል የእናቶችን ድካም የሚያቀልና እንጀራን ከፍ ባለ ደረጃ ማምረት የሚያስችል መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስረድተዋል፡፡

“ማዕከሉ ከፈተናዎቻችን በላይ ሆነን የማይቻል የሚመስለውን የመቻላችን ማሳያ ነው” ብለዋ ፡፡

በየቦታው ያለንን አቅም፣ ገንዘብ እና እውቀት በማስተባበር የነዋሪዎችን ሸክም የሚያቀሉ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ እየተገበርን ነው ሲሉም  ገልጸዋል፡፡

የእንጀራ ማዕከሉ ከ2 ሺህ እናቶች በተጨማሪ በተለያዩ የስራ መስኮች ለ1ሺህ ነዋሪዎች በጠቅላላው ለ3 ሺህ ወገኖች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ የእናቶችን ሸክም በዘላቂነት በሚያቀለው ታላቅ ስራ ላይ ያገዙን ልበቀና ባለሃብቶችን ማለትም ኦቪድ ግሩፕ 170 ሚሊየን፣ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 75 ሚሊየን፣ መድህን ድርጅት 20 ሚሊየን ብር፣ መታሰቢያ ታደሰ ኮንስትራክሽን 500 ዘመናዊ ምጣዶችን በማቅረብ እንዲሁም የታፑ ምግቦች ደግሞ በማማከር ላበረከቱትአስተዋጽኦ ከንቲባ አዳነች በእናቶቹ ስም አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ከንቲባ ጽህፈት ቤት

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ግርማን አልተረዱትምና በሐሳብ ሞግተው ማሸነፍ ሲችሉ ውድ ልጃችንን ነጠቁን” አቶ መካሻ ዓለማየሁ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ
Next article“የሠራተኞችን ጥያቄ ለመመለስ መንግሥት ጥረት እያደረገ ነው” የሥራና ክህሎት ሚንስቴር