
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) እርሱ ቢያልፍም የሚከተለው መርሕ ሁልጊዜ የሚናገርላት ኢትዮጵያና ቆራጥ የኾነው ሃሳቡ ከእኛጋር አብሮ ይኖራል ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡
“ሁልጊዜም ሀገር የምትገነባው በሚሠሩና በሚሰዉ ልጆቿ ነው” ነው ያሉት፡፡ የሚሠሩ ልጆቿ ወደ ላይ ያለውን ይገነቡታል፣ የሚሰዉት ልጆቿ ደግሞ የተገነባውን ሁልጊዜ በደማቸው ይጠብቁላታል፣ ሀገር በዚህ መልክ ነው እስከዛሬ የተጓዘችው፣ ወደፊትም የምትጓዘው ብለዋል፡፡
እጅግ መራራ የኾነ ሀዘን ቢሰማንም ለእውነት፣ ስለእውነት እና ለአመነበት ነገር የሚሰዋ ሰው ስንሸኝ ውስጣችን ቁጭትና ነገ ምን ማድረግ አለብን የሚል ወኔ እንጂ የልበ ደከማ ሃሳብ እንደማይኖረን የታመነ ነውም ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!