
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ አቶ ግርማ ሰውን ለመተዋወቅ ማንነትን፣ ደንበር እና አካባቢን አያይም ይልቁንም ኢትዮጵያዊነትን የሚያስቀድም ታላቅ ፍቅር ያለው ወንድም ነውም ብለዋል፡፡ በዓላማው ጽኑ ፣ በአመነበት ጉዳይ ላይ አቋሙን የማይሸራርፍ፣ የሚመክር፣ ለሕዝብ እና ለሀገር የሚጠቅሙ ሃሳቦችን ወደፊት የሚያመጣ ወንድም ነበር ብለዋል፡፡
አቶ ግርማ ሰዋዊ ባሕሪው ተጨዋች የኾነ ወንድም ነው፡፡ ያዘነን የሚያጽናና ጨለማ የሚመስሉ ጉዳዮችን የሚፈታ ወደ ደስታ የሚቀይር ወንድም ነውም ብለዋል፡፡ የሚያግባቡ ሃሳቦችን በማምጣት እና የጋራ ሚዛናዊ ጉዳዮችን በማንሳት ጉዳዮችን ጉልህ ሚና የሚጫወት ወንድም ነውም ብለዋል፡፡
ወንድማችን ግርማ የሞተው በያዘው ሃሳብ እና ዓላማ ነው፡፡ ይህ ሐሳብ አይሞትም ነው ያሉት፡፡ ሐሳቡ የሚሞት ስላልኾነ፣ የግርማን ሕያውነት የምናረጋግጠው ለሕዝብ የላቀ ጥቅም በመትጋት ነው ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!