
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ የነበሩት የአቶ ግርማ የሺጥላ የህይዎት ታሪክ።
➨ግርማ የሺጥላ ከአባታቸው ከአቶ ሺጥላ ወልደጻድቅ ከእናታቸው ከወይዘሮ ዘውዴ ስመኝ በቀድሞ ሸዋ ክፍለሀገር በመንዝ ግሽ አውራጃ በጌራ ምድር ወረዳ ማሀል ሜዳ ከተማ ሕዳር 17/1967 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
➨የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማሀል ሜዳ አጠናቀዋል፡፡
➨በዲፕሎማ በማኜጅመንት ተመርቀዋል፡፡
➨የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ አግኝተዋል፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በኮተቤ ሜትሮ ፖሊታንት ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ ተመርቀዋል፡፡
➨ሰኔ 1986 በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን በአንጾኪያ ወረዳ የተፈጥሮ ሀብት ጽሕፈት ቤት ባለሙያ ኾነው ሠርተዋል፡፡
➨1989 ጀምሮ እስከ 1990 ዓ.ም ድረስ በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን በአንጾኪያ ወረዳ የኢኮኖሚ ዘርፍ ሥራ አሥፈጻሚ በመኾን አገልግለዋል፡፡
➨1990 ዓ.ም እስከ መስከረም 1995 ዓ.ም የአንጾኪያ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ በመኾን አገልግለዋል፡፡
➨1995 ዓ.ም የሰሜን ሽዋ ዞን ብአዴን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኾነውም አገልግለዋል፡፡
➨ከመስከረም 1997 ዓም እስከ ሕዳር 30/1998 ዓ.ም የደብረብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የማስታወቂያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ በመኾን ሠርተዋል፡፡
➨ታኅሣሥ 1/1998 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ሽዋ ዞን የባሶና ወረና የማስታወቂያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመኾን ሠርተዋል
➨ሚያዚያ 1/1999 እስከ መስከረም 2000 ዓ.ም ድረስ የሰሜን ሽዋ ዞን የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ኾነው ሰርተዋል፡፡
➨የሰሜን ሽዋ ዞን የብአዴን ጽሕፈት ቤት የሕዝብ አደረጃጀት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኾነውም ሠርተዋል፡
➨እስከ መስከረም 2008 ዓ.ም ደግሞ የሰሜን ሽዋ ዞን ምክትል አሥተዳዳደሪ በመኾንም ሠርተዋል፡፡
➨ከጥቅምት 1/2008 ዓ.ም ጀምሮ የሰሜን ሽዋ ዞን አሥተዳዳደሪ በመኾንም ሠርተዋል፡፡
➨በ2013 ዓ.ም የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ ኾነው አገልግለዋል፡፡
➨ከመስከረም 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሕይወታቸው አስካለፈበት ቀን ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም ጀምሮ የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ በመኾን አገልግለዋል፡፡
➨በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በባሶና ወረና ወረዳ የቀይት ምርጫ ጣቢያ በመወዳደር ሕዝባቸውን ወክለው ሲሠሩም ቆይተዋል፡፡
➨የአማራ ክልልን በመወከልም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል ኾነው ሠርተዋል፡፡
➨ከመደበኛ ሥራቸው ጎን ለጎን የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ፣የደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል እና የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽኝ ሥራ አመራር ቦርድ ኀላፊ ኾነውም ሠርተዋል፡፡
➨አቶ ግርማ የሽጥላ በ48 ዓመታቸው በተፈጸመባቸው ግድያ ህይዎታቸው አልፏል፡፡
➨አቶ ግርማ የሺጥላ የ3 ሴቶች እና የ4 ወንድ ልጆች አባትም ነበሩ፡፡
በምሥጋናው ብርሃኔ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!