
✍ የጋራ እሴቶቻችን ለማሳደግ እንታትራለን፣ በሴራ ምሳር ቀስ እያለ እሴቶቻችን ለመመንጠር የሚሠራ ደግሞ አለ፡፡ ከሠራን ምሳሩ ሊያስቆመን አይችልም፣ እኛ ካልሠራለን እንጠፋለን፡፡
✍ ካባቱ ያልበለጠ ትውልድ እንዳልተወለደ ይቆጠራል፣ ትውልድ እንሁን፤ ትወልድስ እንዴት ማስቀጠል እንችላለን? የሚለው የቤት ሥራ የእኛ ነው፡፡
✍ ሰው እንደ ሰው ለመደማመጥ ለመነጋገር የሚያስችለው ዋነኛው ጉዳያችን አፍረሰናል፣ መደማመጥ አልቻልንም፣ ለመደማመጥ መዘጋጀት አለብን፣ መደማመጡ ደግሞ ልብ ለልብ መሆን አለበት፣ ከልብ መደማመጥ ካልቻልን የትም አንደርስም፤ ባለ መደማመጥ ምክንያት የችግር መፍቻው ኃይል፣ ጉልበት፣ ጦርነት እየሆነ መጥቷል፤ የችግር መፍቻችን አንዱ አንዱን ማጥፋት ሆኗል፣ አውዳሚ ወደ ሆነ ጉዳይ እየተሸጋገርን ነው፤ ይሄን ጉዳይ መቋጨት አለብን፣ ችግሩ እንዲቋጭ ደግሞ ሁሉም በሰከነ መንገድ ተነጋግሮ፣ ችግሩን መርምሮ መፍትሔውን ማስቀመጥ አለበት ብለው ነበር፡፡
✍ በመጀመሪያ ከራሳችን ጋር መግባባት አለብን፣ ቤተሰብ፣ ኅብረተሰብ፣ ሕዝብ ብሎ ሀገራዊ መግባባት አለብን ነበር ያሉት፡፡ አባቶቻችን ካስቀመጡን ከፍታ ላይ ሆነን እንዴት እንነጋገር? ምን ነክቶን ነው ምን እናድርግ? ማለት ይገባናል፡፡
✍ ችግቻችን ለመፍታት እንችልም እንዳንል ችለን ያለፍናቸው ነገሮች አስገራሚና አስደናቂዎች ናቸው፣ ከማንም በላይ ነጻነትን ያለመስጠት፣ ለነጻነት መሞት፣ ለነጻነት መስዋእትነት የመክፈል ጦርነቶችን አካሂደን ድል አድርገናል፤ ነጻነታችን አስከብረናል፡፡ አሁን ታዲያ ለምን ነጻነቱን እንፈልገዋን? እርስበርሳችን ልነገዳደል ልንጠፋፋ ከሆነ ስለ ምን እንፈልገዋን?
✍ አሸናፊዎች ለመሆን መጀመሪያ እያንዳንዱ ሰው ራሱን ማሸነፍ አለበት ብለውም ነበር፡፡ የሴራ መጥረቢያው መንጥሮ መንጥሮ በሠራው ሥራ ዝቅ ስትሉ መሪ መሆናችሁን የሚከብድ ነገር ይገጥማችኋል፡፡ ቀበሌ ላይ ሄዳችሁ ስታወያዩ፣ ቀበሌው በአግባቡ ተመርቷል ወይስ አልተመራም አይደለም ጥያቄው የእኛ ቀበሌ በእኛ ሰፈር ለምን አይመራም የሚል ነው፤ ይህ አደገኛና አውዳሚ አካሄድ ነው፡፡
በሀሳብ ተበትነናል፣ ወደ አደጋ ሳንሄድ ካልሰበሰብነው ችግር ነው ብለውም ነበር፡፡