
በወንድማችን በግርማ የሺጥላ ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት በእጅጉ አዝኛለሁ። የዚህ አሰቃቂ ድርጊት ዓላማ ለሀገር የሚሠሩትን ማሸማቀቅ ነው። ግን አይሳካም። ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን የኢትዮጵያ ጉዞ አይገታም።
ይሄንን ኢሰብአዊ ድርጊት የፈጸሙትን አካላት ለፍርድ ለማቅረብ እየሰራን ነው። ኢትዮጵያ የጽንፈኞች ሀገር እንዳትሆንም ሕግ ማስከበራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
ለጓዶቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ፣ ቤተሰቦቹ እና ለመላው ሕዝብ መጽናናትን እመኛለሁ።