
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና መሬት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች፤ በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ድንገተኛ ህልፈተ ሕይዎት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
በተመሳሳይ፤ የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ሚያዝያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ በጉዞ ላይ በነበሩት የአማራ ክልል ብልጽግና ፖርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላና አብረዋቸው በነበሩ ወንድሞች ላይ በደረሰው የሞት አደጋ ከፍተኛ ድንጋጤና ሃዘን እንደተሰማው ገልጿል።
ጉባዔው ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል። ለሟቾችም ዕረፍተ ነፍስን ተመኝቷል።