“የጽንፈኝነትን ሰይጣናዊነት ያሳየ የግፍ ግድያ” የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

117

ጽንፈኝነት ብዙዎችን ሕዝብ ልጆች አሳጥቶናል። ጽንፈኞች ሰው ሆንን ይጠፋሉ።
ዛሬ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ግርማ የሺጥላ ባደገበት ቀየ በጽፈኞች በግፍ ተገድሏል። ይህም የጽንፈኛው ኃይል የመርዝ ፖለቲካ በቀየ የማይወሰን፣ ከጓዳ ጭምር ገብቶ ቤተሰብን የሚበትን ሆኑን አሳይቶናል።
ውዱ የኢትዮጵያ ሕዝብ!
አጀንዳ አልባ የጥላቻ ፖለቲካ ዘርተው ጽንፈኝነት በማብቀል ልጆችህን በአደባባዩ የሚቀጥፉ የደም ነጋዴዎችን ማስቆም ካልቻልክ፣ የግፍ በትራቸውን የብዙኃኑን ቤት ማንኳኳቱ አይቀሬ ነው።
ዓላማቸው ማተራመስና ሀገራችንን ዕረፍት መንሣት የሆኑ አካላት አሉ። የእነዚህ አካላት አርአያዎቻቸው ዓለም አቀፍ አሸባሪዎች ናቸው። የእነርሱን ተግባር በኢትዮጵያ ለመድገምና ኢትዮጵያን ለማጥፋት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ያልተፈጸሙ ዘግናኝ ተግባራትን ሁሉ ይፈጽማሉ።
ኢትዮጵያን ለማጽናትና ለማበልጸግ የጀመርነውን ትግል ጽንፈኞች አያስቆሙትም። ይሄንን ነውረኛ ዘግናኝ ተግባር የፈጸሙት የትም ቢገቡ ለሕግ ይቀርባሉ። ሌሎች በእነርሱ መንገድመ ጓዝ የጀመሩ በሕግ ማስከበር እዲቆሙ ይደረጋል።
ነብስህ በሰላም ትረፍ!
ሚያዝያ19/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Previous articleከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ
Next articleየሀዘን መግለጫ