ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

181

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመረጡ፡፡ በዛምቢያ ሉሳካ ሲካሄድ የቆየው የኮንፌዴሬሽን ኦፍ አፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ ዛሬ ተጠናቋል፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ በካውንስሉ በሙሉ ድምፅ መመረጣቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article50 ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት የኢትዮጵያን ድጋፍ መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next articleበማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀሙሲት ከተማ በ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ሊገነባ ነው፡፡