
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 50 ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስውጣት በሚያደርጉት ጥረት ኢትዮጵያ ድጋፍ እንድታደርግ በይፋ መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በሱዳን ቀውስ ሳቢያ የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን የማስውጣት ስራ ጋር በተያያዘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ለተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም 50 ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት በሚያደርጉት ጥረት ኢትዮጵያ ድጋፍ እንድታደርግ በይፋ መጠየቃቸውን ገልጸዋል።
ይህን ተከትሎም ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር በአየር እና በየብስ ዜጎችን ለማስወጣት ጥረት መደረጉን ገልጸዋል።
አምባሳደሮቹ በበኩላቸው፤ በሱዳን ሁሉም ወገን ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጣና አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ያሉ የውጭ ሀገራት ዜጎችን በማስወጣት ሥራ ላይ ኢትዮጵያ እየተጫወተች ያለውን ሚና አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!