በሴካፋ ውድደር የሚጫወቱት ሉሲዎቹ ወደታንዛኒያ አቅንተዋል፡፡

158

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ውድደር ኢትዮጵያ ትሳተፋለች፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ዛሬ ጠዋት ወደታዛኒያ ዳሬሰላም አቅንተዋል፡፡
ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሴቶች የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ዘንድሮ ታንዛንያ ስታስተናግደው ስምንት ሀገራት ይሳተፉበታል፡፡ በአዲሱ አሰልጣኝ ብርኃኑ ይግዛው የሚመሩት ሉሲዎቹ ልምምዳቸውን በአዲስ አበባ ስታዲዬም ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ሉሲዎቹ በምድብ ሁለት ኬኒያ፣ ጅቡቲና ዩጋንዳ ጋር ተደልድለዋል፡፡
‹‹ሉሲዎቹ ወደስፍራው ያቀኑት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የሴቶች እግር ኳስ ውድድር እና ልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሶፊያ አልማሙን እየተመሩ ነው›› ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በድረ ገጹ አስታውቋል፡፡
በታርቆ ክንዴ

Previous articleየደራ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ፈጣን ምላሽ ባለማግኘቱ ቅሬታውን ገለጸ፡፡
Next articleፕሮጀክቱ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ ትልቅ ሚና አለው ተባለ፡፡