
ደብረ ብርሃን: ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮ ቴሌኮም ማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ሠራተኞችና አጋር ድርጅቶች ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የተፈናቃዮች ጣቢያ ለሚገኙ ዜጎች ድጋፍ አድርገዋል::
የማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ከተማ ዳዲ ከሪጅኑ ቋሚና ኮንትራት ሠራተኞች እና ከሪጅኑ አጋር ድርጅቶች በተሰበሰበ 406 ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር የጤፍ ዱቄት ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል::
ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው የተፈናቃዮች ጣቢያ ለሚገኙ 240 አቅመ ደካሞች ድጋፉ ተሰጥቷል::
ዳይሬክተሩ የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከፍተኛ ከመኾኑ አኳያ ድጋፋችን ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ እኛም አጋሮቻችንም ተረድተናል ብለዋል፡፡ ሌሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶችም ለተፈናቃዮቹ ትኩረት እንዲሰጡም አሳስበዋል::
ድጋፍ የተደረገላቸው ተፈናቃዮችም ኢትዮ ቴሌኮም እና አጋሮቻቸው ስላደረጉላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።
ዘጋቢ፦ ሥነ ጊዮርጊስ ከበደ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!