የሚኒስትሮች ምክር ቤት የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ውሳኔዎችን አሳለፈ።

72

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ምክር ቤቱ በመካከለኛ ዘመን /2016-2020/ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ነው ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈው፡፡

ማዕቀፉ በዋናነት የመንግስት በጀት ከማክሮ ኢኮኖሚ ዓላማዎችና ታሳቢዎች ጋር ተጣጥሞ እንደተዘጋጀ የሚያመላክት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም የመካከለኛ ዘመን የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲሁም የፊሲካል ሚዛን የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመለየትና ለማመላከት የሚያገለግል የበጀት ዕቅድ መሳሪያ ሆኖ የ2016 የፌዴራል መንግስት ዝርዝር በጀት የሚዘጋጅበትን ጥቅል የገቢ ትንበያ፣ የወጪ ጣሪያ፣ የክልላዊ መንግስታት የበጀት ድጋፍ ጣሪያና የፊሲካል ጉድለት መጠንን የሚያመላክት ሆኖ መዘጋጀቱን ምክር ቤቱ አረጋግጧል፡፡

ማዕቀፉ ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት የተጋረጠውን የፊሲካል ስጋት ለመቅረፍና የፊሲካል ጤናማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የፋይናንስ አጠቃቀም ስልት ተግባራዊ እንዲደረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
ስለሆነም ማዕቀፉ የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲመጣጠን ማድረግን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ምክር ቤቱ በማዕቀፉ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጎንደር በረሀማ አካባቢዎች የሚገኙት የ “በጋይት” ዝርያ ያላቸው ላሞች፣ ከፍተኛ የወተት ምርት እየሰጡ ነው፡፡
Next articleበብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርእሳነ መስተዳደር ልዑካን መቀሌ ገቡ።