“የዒድ አልፈጥር በዓልን ማንነታችን ተከብሮ በነፃነት እያከበርን ነው ” የአላማጣ ከተማ የእስልምና እምነት ተከታዮች

101
ወልድያ: ሚያዝያ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 444ኛው ዒድ አልፈጥር በዓል ካለፈው ዓመት ወዲህ ከስደትና እንግልት መልስ ከቤተሰቦቻችን ጋር በድምቀት የምናከብረው ነው ሲሉ የአላማጣ ከተማ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡
በዓሉን ምስኪኖችን በማሰብ፣ በመተዛዘን፣ በመረዳዳትና ከክርስቲያን ቤተሰብና ጎረቤቶች ጋር በአብሮነት እናከብራለን ሲሉ ምዕመናኑ አስረድተዋል።
አሚኮ ያነጋገራቸው የከተማዋ ሙስሊም ማኀበረሰብ አባላት ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መልካም ምኞትን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦ ካሳሁን ኃይለሚካኤል
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“በረመዷን የተፈቀደውን እንዳያደርግ የተከለከለ ከረመዷን በኋላ ያልተፈቀደለትን ነገር መዳፈር አይፈቅድለትም” ኡስታዝ በድሩ ሁሴን
Next articleበሮመዷን የነበረው የሰላም፣ የአንድነት፣ የእዝነትና የመረዳዳት ምግባር በቀጣይም ሊተገበር እንደሚገባ የደብረታቦር ከተማ ሙስሊሞች ተናገሩ፡፡