“እንኳን ለዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!” ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ

85

“እንኳን ለዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!” ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

ርእሰ መሥተዳድሩ ያስተላለፉት ሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ቀጥሎ ይቀርባል።

እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ አል ፈጥር ዕዝነት፣ ርህራሄ፣ መተሳሰብ፣ መደጋገፍና አንድነት የሚጠናከርበት ነው። ያለው ለሌለው በማካፈል በጋራና በደስታ የሚከበር በመሆኑ የአብሮነት መገለጫም ነው። ደስታን ለሌሎች ማጋራት ደግሞ የኃይማኖቱ መልካም አስተምሮ በመሆኑ እሴቱ ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

የረመዳን ፆም ሃይማኖታዊ ሥነ-ምግባርን ጠብቆ የሚፆም ታላቅ ወር በመሆኑ የዒድ-አልፈጥር በዓልን ስናከብርም ሃይማኖታዊ ሕግጋቱ በሚፈቅደው መሰረት ለአካባቢያችን ሰላም በጋራ ዘብ በመቆም ሊሆን ይገባል።

በዓሉን ስናከብር የቆየውን የመደጋገፍና የመፈቃቀድ እሴቶቻችንን በማጠናከር፣ የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብ እንድናሳልፍ ጥሪ እያቀረብኩ፤ በድጋሜ እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ!

ዒድ-ሙባረክ!

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“እንኳን ለ1444 ኛው የዒድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሣችሁ! ዒድ -ሙባረክ 🕌”የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ
Next articleእሙ አይመን – የጀነት ሴት!