በተርኪዬ የሚማሩ ኢትዮጵያውያን የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በኮምቦልቻ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

80

ደሴ: ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከ600 ሽህ ብር በላይ የሚገመት ደጋፍ በካዳም መረዳጃና የልማት ማኅበር አማካኝነት ለተፈናቃዮች ደርሷል፡፡

ድጋፉ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የተከናወነ ነው፡፡ የከዳም መረዳጃና የልማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ኡመር ብርቁ የኢድ አልፈጥርን በዓል ምክንያት በማድረግ ቱርኪዬ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የተሰባሰበውን የምግብ ቁሳቁስ በአካል ተገኝተው አስረክበዋል፡፡ ድጋፉም ከ600 ሺህ ብር በላይ እንደሚገመት ገልጸዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አቶ ሙሐመድአሚን የሱፍ በበኩላቸው በከተማዋ ከ 6 ሽህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ገልጸው፤ ሁሉም ወገን ድጋፍ እንዲያርግ ጠይቀዋል፡፡ አቅመ ደካሞችና ተፈናቃዮች የኢድ አልፈጥር በዓልን በደስታ እንዲውሉ ማድረግ ከሁላችንም ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡ ለተደረገው ድጋፍም አመስግነዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው ተፈናቃይ ወገኖችም ብዙ የለመደ እጃቸው ዛሬ ላይ በጊዚያዊነት መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡ ለተደረገላቸው ድጋ ያመሰገኑት እነዚሁ ተፈናቃዮች ከችግራቸው በዘላቂነት እንዲላቀቁ አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግላቸው ጠጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ደጀን አምባቸው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዒድ አልፈጥር በዓል የሚከናወኑ ተግባራትና ሃይማኖታዊ አስተምህሮው”
Next articleለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ኢድ ሙባረክ!!