“በኢትዮጵያ እና በሱዳን ወንድማማች ሕዝብ መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የሚሠሩ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

52

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን ወንድማማች ሕዝብ መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የሚሠሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓረብኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልእክት፣ የሱዳን እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ብዙ ፈተናዎችን እየተጋፈጡ በሚገኙበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የሐሰት ውንጀላዎችን በማሰራጨት የፖለቲካ ዓላማቸውን ለማሳካት የሚጥሩ ወገኖች እንዳሉ ጠቁመዋል።

እነዚህ ወገኖች ኢትዮጵያ ጦሯን ወደ ሱዳን ድንበር አካባቢ አስገብታለች እያሉ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን መልካም ጉርብትና እና ግንኙነት ለማበላሸት ዓላማ ያላቸውን እነዚህን ውንጀላዎች አጥብቀን እናወግዛለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት መካከል ላለው ወንድማማችነት እና መልካም ጉርብትና ዋጋ የምትሰጥ በመሆኗ የሁለቱ ወንድማማች ሀገሮች የድንበር ጉዳይ በውይይት እና በውይይት ብቻ እንደሚፈታ በፅኑ እንደምታምን ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሥራ መብዛት ጾሙን አላስተጓጎለውም እንዲያውም እንድንጠነክር አገዘኝ እንጅ” ወይዘሮ መሬም ማሩ
Next article“የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ሥራ ተገብቷል” የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል