“የዜጎችን ጥቅም፣ መብትና ደኅንነት ማስከበር እንዲቻል ሀገራት ጋር ንግግር ከማድረግ ባሻገር ውል ተዋውያለሁ” የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

76

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መብት፣ ደኅንነትና ጥቅሞቻቸው እንዲከበሩ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ገልጿል።

ከሰሞኑ በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የተመራ ልዑክ በቤሩት፣ ሊባኖስና ሳዑዲ አረቢያ ተዘዋውሮ ሥራዎች መሥራቱን ሚኒስትሯ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ አንስተዋል።

“በሳዑዲ አረቢያ በነበረን ቆይታ ከፍተኛ የሠራተኛ ፍላጎቶች መኖራቸውን አይተናል” ያሉት ሚኒስትሯ ሆኖም ሠራተኞች የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈላቸው፣ በወቅቱ እንዲከፈላቸውና ሰላምና ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ ተነጋግረናል ብለዋል።

እነዚህ ሁነቶች በተለይ ከዚህ በፊት የነበረው ሠራተኞች በሕገወጥ መንገድ እየኖሩ ከለላ እንዳይኖቸው ይደረጉ የነበሩበትን ችግር ይቀርፋል ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

94 ሥርዓተ ስልጠና ማዕከላት ተከፍተው ለዜጎች የክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ በተለይም ሕገወጥ ፍልሰትን በመከላከል ዜጎች በሕጋዊ መልኩ ወደ ሌሎች ሀገራት ሄደው እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል። እስካሁንም በተለያዩ ዙሮች ስልጠናዎች እየተሰጡ ነውም ተብሏል።

እንደ ሀገር እስካሁን ህጋዊ ውል ያለው ከ ከጆርዳን፣ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከኳታር እና ከዩናይትድ አረብ ኢሚሬቶች እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሚኒስትሯ አሁንም በአፍሪካና በአውሮፓ ጭምር የመዳረሻ ሀገራት እየመጡ ውል እየተወሰደና ስልጠናው እየተሰጠ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ እንዳልካቸው አባቡ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck

Previous article“ዘካተል ፊጥር ከዒድ በፊት የሚከወን አቅመ ደካሞች በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ የሚሰጥ ስጦታ ነው” የአፋር ክልል የቀድሞ ሸሪዓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
Next article“የሥራ መብዛት ጾሙን አላስተጓጎለውም እንዲያውም እንድንጠነክር አገዘኝ እንጅ” ወይዘሮ መሬም ማሩ