
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በስምምነቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቀበታ እንዳሉት የአጋርነት ስምምነቱ ወረቀት አልባ የጉምሩክ አገልግሎቱን ለማሳደግ፣ በቴክኖሎጂ የአሠራር ዘዴዎችን ለመቀየር እና በዘመናዊ አከፋፈል የከፋይ ጊዜን እንዲሁም ድካምን ለመቆጠብ ያግዛል።
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የአጋርነት ስምምነቱ በዋነኛነት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በዲጅታል የታገዘ የአገልግሎት ሥርዓት በመዘርጋት የታክስና ቀረጥ ክፍያዎችን በቀላሉ ለመሰብሰብ እንደሚያግዘው ተናግረዋል፡፡ ስምምነቱ የኮሚሽኑ ደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ ትልቅ ሚና እንዳለው ሥራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡
የጉምሩክ ታክስ እና ቀረጥ ክፋያዎች በቴሌ ብር መደረጉ ለሀገር ከሚሰጠው ጠቀሜታ ባሻገር የሎጂስቲክ አፈጻጸም ጠቋሚ እንዲሻሻልና ለመጋዘን የወደብ ኪራይ የሚከፍሉ ወጭዎችን ለመቀነስ አስተዋፅኦው የጎላ ነው ተብሏል፡፡
ዘጋቢ፡- ራሄል ደምሰው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!