የሕዳሴ ግድብን በፍጥነት ማጠናቀቅ የሚነሱ ውዝግቦችን ለመቋጨት ያግዛል ተባለ፡፡

127

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 28/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ለመገናኛ ብዙኃን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በግድቡ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በመግለጫው የሕዝቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነግሯል፡፡

ከሕዝቡ ተሳትፎ ግድቡ ከተጀመረ አንስቶ 13 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡና በተያዘው በጀት ዓመት ሩብ ዓመት ብቻ ደግሞ 168 ሚሊዮን 952 ሺህ ብር መሰብሰቡ በመግለጫው ተመላክቷል፤ በመስከረም ወር ብቻ 82 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡም ታውቋል፡፡ ወደ ፊትም የሕዝቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እንደሚጠበቅና ለዚህም እንደሚሠራ ተመላክቷል፡፡

የሕዝቡን ተሳትፎ ለማስቀጠል የመገናኛ ብዙኃን ሕዝቡን እንዲቀሰቅሱም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የሦስትዮሽ ግንኙነት በሠላማዊ መንገድ መቀጠሉም በመግለጫው ተነስቷል፡፡

በግድቡም ሆነ በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑም ተመላክቷል፡፡ አንድ በመሆንና በመተባበር ግድቡን ፈጥኖ መጨረስ በግድቡ ዙሪያ ለሚነሱ ውጣ ውረዶች ትላቅ መፍትሔ ነውም ተብሏል፡፡
ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ -ከአዲስ አበባ

Previous articleየቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳሲልቫ ከእስር ሊፈቱ ይችላል ተባለ፡፡
Next articleአሜሪካ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች የስልጣን መጋራት ጊዜውን መግፋታቸው እንዳሳሰባት ተናገረች፡፡