“ወገን በተግባር የተገለጠ አለኝታነቱን አሳይቶናል” በደብረ ብርሃን የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች

71
ደብረ ብርሃን: ሚያዝያ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረብርሃን ከተማ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖችን የማግደፍ ሥራ በበጎ አድራጊ ወገኖች ተከናውኗል።
መኖሪያቸውን በውጭ ሀገር ያደረጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያሰባሰቡትን ገንዘብ በመላክ ተፈናቃይ ወገኖች በዓልን ተደስተው እንዲያሳልፉ አድርገዋል።
የተሰበሰበውን ድጋፍ በመያዝ ለተፈናቃይ ወገኖች ያስረከበችው ሙልዬ ንጋት የትንሣኤ አስተምሮ መስዋዕትነት እና ለሰው በጎ ማድረግ በመኾኑ በጎ አድራጊ ግለሰቦች ባበረከቱት ድጋፍ ተፈናቃይ ወገኖች በዓልን በደስታ እንዲያሳልፉ ማድረግ ተችሏል ብላለች።
ከ30 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች የተጠለሉባት ደብረ ብርሃን ከተማ ተፈናቃዮችን በተለያዩ ካምፖች አስጠልላለች።
አሁን ላይ በከፍተኛ ችግር ውስጥ መኾናቸውን ለአሚኮ የተናገሩት እነዚህ ወገኖች፤ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ለተደረገላቸው የማዕድ ማጋራት መርሃግብር አመስግነዋል።
በጎ አድራጊ ወገኖች 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በማሰባሰብ ነው ማዕድ ያጋሩት። ለእስልምና እምነት ተከታዮች ማፍጠሪያ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ደግሞ የበዓል መዋያ ማዕድ ነው ያጋሩት። ተፈናቃይ ወገኖች ያሉበት ሁኔታ የከፋ በመኾኑ ሌሎች ወገኖችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ዘጋቢ፦ ኤልያስ ፈጠነ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከከተማ አሥተዳደሩ እና ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር የትንሣኤን በዓል አከበሩ።
Next articleየደብረታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከማንኛውም የፕላስቲክ አይነቶች ነዳጅ በመፍጠር ለዕይታ አቀረበ።