
ደሴ: ሚያዝያ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መካላከያ ሠራዊት አባላት ኅብረተሰቡ በዓሉን ከነሱ ጋር አብሮ በማሳላፉ መደሰታቸውን ገልፀዋል።
በዝግጅቱ ላይ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፋት የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሀመድ አሚን የሱፍ የመከላከያ ሠራዊት እና የኮምቦልቻ ከተማ ሕዝብ ትናንት አብሮ የመከራ ጊዜን ያሳለፈና ነገም በአብሮነት እስከመጨረሻው የሚቀጥል የአንድነት ማሳያ ነው ብለዋል።
በእናንተ መስዋእትነት እኛን አኑራችሁናል ያሉት ከንቲባው ፤ የናንተን ውለታ መቸም አንከፍለውም ብለዋል።
የኛ መነገድም ማትረፍም ያለ እናንት መስዋትነት የማይታሰብ ነው ያሉት የኮምቦልቻ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ፕሬዝዳንት ኑሬ ሰይድ፤ ዛሬ የንግዱ ማኅበረሰብ ያደረገው ጥቂቱን ግን የሚገባችሁን በማለት ለሠራዊቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
በኮምቦልቻ ከተማ የተርክ ካምፕ ሆስፒታል ኀላፊ ኮ/ል ተፈራ የሽዋስ፤ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር እና የንግዱ ማኅበረሰብ በዓሉን ከሠራዊቱ ጋር አብሮ በማሳለፋ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የኮምቦልቻ ማኅበረሰብ ትናንት አብሮነቱን በደጀንነት በግንባር ያስመሰከረ ሕዝብ ነው፤ ዛሬም አብሮነቱን ስላሳየን በሠራዊቱ ስም እናመሰግናለን ብለዋል።
ማኅበረሰቡ በዓልን እቤታችን እንዳለን እንዲሰማን በማድረጉ ደስታ ተሰምቶናል ሲሉ የመከላኪያ ሠራዊት አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ አበሻ አንለይ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!