“11ሰዓት ሲሆን የእየሱስ ስጋ ወደ መቃብር የወረደበት ጊዜ ነበር” የቅኔ እና የአዲስ ኪዳን መምህር ጥቀኄር ወርቄ

146
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) እለተ አርብ እንደ ሁለት ቀን ተቆጥራለች። ከጠዋት እስከ ስድስት ሰዓት ቀን እስከ ዘጠኝ ጨለማ አንድ ቀን፡፡ ከዘጠኝ ሰዓት እስከ 12:00 ሰዓት ብርሃን እንደገና ከአስራ ሁለት ሰዓት እስከ ጠዋት አስራ ሁለት ሰዓት ጨለማ ሁለት ቀን፡፡
አስራ አንድ ሰዓት ሲኾን ንጉስ የሠቀለውን ማውረድ አይቻልም እና ዮሴፍ ጲላጦስ ዘንድ ሄዶ እባክህ የጌታን ሥጋ ከመሥቀል አውርጄ ልቅበረው ብሎ ጠየቀ፡፡ ንጉሱ ፈቀደለት፡፡ ዮሴፍ እና ኒቆዲሞስ የጌታን ሥጋ አወረዱት፡፡ ኢየሱስም አይኑን ገለጥ አድርጎ ሲገንዙት እነሆ እንደተራ ሰው ትገንዙኛላችሁን ብሎ ጠየቃቸው ምን እንበል ብለው ጠየቁ ኢየሱስም ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኀያል ቅዱስ ሕያው እንዘይመውት የማይሞተው ሞተ እያላችሁ ገንዙኝ አላቸው። እነሱም “ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው እንዘይመውት” ብለው ገንዘው ወደ መቃብር አወረዱት። ብለዋል መምህሩ፡፡
ዘጋቢ፦ ትርንጎ ይፍሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ዘጠኝ ሠዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ነፍሱ ከቅዱስ ሥጋው የተለየችበት ሠዓት ነው” የቅኔ እና የአዲስ ኪዳን መምህር ጥቀኄር ወርቄ
Next article“በዓሉን ስናከብር የሃይማኖቱን አስተምህሮ በተግባር በመፈጸም መኾን አለበት” መልዓከ ምሕረት ግሩም አለነ