“ዘጠኝ ሠዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ነፍሱ ከቅዱስ ሥጋው የተለየችበት ሠዓት ነው” የቅኔ እና የአዲስ ኪዳን መምህር ጥቀኄር ወርቄ

132
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኝ ሠዓት በኾነ ጊዜ “ሁሉ ነገር ተፈጸመ አለ” እየጮኸ ነፍሱ ከስጋው ተለየች፡፡ አንድም ለሰው ልጆች የገባሁት ቃል ተፈጸመ ለማለት ሲኾን፣ በሌላ በኩል በነቢያት የተነገረው በሀዋርያት የተጻፈው ሁሉ ተፈጸመ ማለት ነው፡፡ አዳምም ዳነ እኔም ተሠቀልኩ ማለቱ ነው፡፡ በዘጠኝ ሠዓት የኢየሱስ ክርስቶስ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ቅድስት ነፍሱ ከቅድስት ሥጋው ተለዬች፡፡
ኢየሱስ ለንጊኖስ የሚባል አንድ አይኑ የጠፋ አይሁድ ወዳጅ ነበረው፡፡ ለንጊኖስ በክርስተስ ሞት በምክሩም በሞቱም አብሮ አልተሳተፈም ነበር፡፡ ዘጠኝ ሠዓት ሲኾን ለንጊኖስ ፈረስ ላይ ኾኖ ቀራንዮ ደረሰ፡፡ በወቅቱም አካባቢው ጸጥ ብሎ ነበርና ጌታዬ ሞተሃል? ወይስ አለህን? ብሎ በያዘው ጦር ጎኑን በወጋው ጊዜ በ”ለ” ቅርጽ ውኃ እና ደም ፈስሷል ይህም ለዓለም ድኅነት ተሰጥቷል፡፡ የተፈናጠረው ደም የለንጊኖስን አይን አብርቶለታል፡፡ ለንጊኖስ ወገኖቹ አይሁዳን ይኹኑ እንጅ ለጌታ ወዳጁ በመኾኑ ኢየሱስ ይህን አደረገለት ብለዋል መምህር ጥቀኄር፡፡
ከወንበዴዎች ይቆጠራል ተብሎ የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ኢየሱስ በሁለቱ ወንበዴዎች መካካል ተሠቀለ፡፡
ኢየሱስ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን ከመበርበሩ በፊት በቀኙ የተሠቀለው ወንበዴ አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ ብሎት ነበር፡፡ በዚህ ሰዓት አንተ ከአዳም ቀድመህ ገነት ትገባለህ አለው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋው በመሥቀል ላይ እያለ ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ በሲኦል በር ላይ የተወጋ ቀኝ እጁን አሳያቸው፡፡ ደመ ማኅተሙ ጥምቀት ኾኗቸው አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በሲኦል በአጋንንት እግር ሲረገጡ የቆዩት የአዳም እና የሄዋን ልጆች ነፍስ ይዞ ወጣ፡፡ “ቀኝ እጄን ሠጠኋቸው እነሱም ተጠመቁ አለ ክርስቶስ” ያወጣቸውን ነፍሳት ቀድመኽ ገነት ትገባለህ ለተባለው ፈያታዊ ዘየማን ደመ ማኅተሙን ሠጠው እና ወደ ገነት ወሰዳቸው፡፡ የገነት ጠባቂው ሱራፌል ደነገጠ አንተ ማነህ ከቀደሙ ነብያት እየጠራ ጠየቀው እኔስ የሰው ደም ሳፈስ የኖርኩ ምድረ ኢየሩሳሌምን ስበጠብጥ የኖርሁ ሽፍታ ነኝ ነገር ግንጌታ በተሠቀለ ሠዓት በመንግሥትህ በመጣሕ ጊዜ አስበኝ በማለቴ ይህን ክብር አገኘሁ እንጅ ሲል እንደመለሰለት እና ቀድሞ ገነት እንደገባ መምህር ጥቁኄር ነግረውናል፡፡ የንጉስን ማኅተም የያዘ የታመነ ነው እና ነፍሳትን እየመራ ወደ ገነት ገባ፡፡
ዘጋቢ፦ ትርንጎ ይፍሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ኢየሱስ በስድስት ሠዓት ሲሆን ቀራንዮ ላይ ተሰቀለ” የቅኔ እና የአዲስ ኪዳን መምህር ጥቀኄር ወርቄ
Next article“11ሰዓት ሲሆን የእየሱስ ስጋ ወደ መቃብር የወረደበት ጊዜ ነበር” የቅኔ እና የአዲስ ኪዳን መምህር ጥቀኄር ወርቄ