
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሣምንት ጨዋታ ባሕርዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 አሸነፈ፡፡
ባሕዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ 9፡00 ላይ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡
በዚህም ሀብታሙ ታደሠ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች እና ዱሬሳ ሹቢሳ በሁለተኛው አጋማሽ ባስመዘገባት አንድ ግብ ባሕርዳር ከተማ ማሸነፍ ችሏል፡፡
የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ ግብ በሁለተኛው አጋማሽ ቢንያም ጌታቸው አስቆጥሯል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!