የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ።

191
አዲስ አበባ: ሚያዝያ 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሯ አዲስ አበባ ሲገቡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ለሁለት ቀናት ቆይታ የሚያደርጉ ሲኾን በዚህም ከኢፌዴሪ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና ከአፍሪካ ኅብረት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ኢትዮጵያ እና ጣሊያን ባላቸው ሁለትዮሽ እና የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ፣ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።
በሌላ በኩል የሚኒስትሯ ጉብኝት ጣሊያን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ሰብአዊ እና የልማት ድጋፍ ማጠናከር እንደሚኾን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለፁ የሚታወስ ነው።
ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የትንሣዔ በዓልን ስናከብር የሀገር አንድነትን በዕርቅ ዘላቂ ለማድረግ ቃል በመግባት መኾን አለበት” የእምነት አባቶች
Next articleሁሉ ተፈጸመ!