
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕርዳር ከተማ የእርድ እንስሳት አቅርቦት ቢኖርም ከባለፉት በዓላት ከነበረው ዋጋ ጭማሬ ማሳየቱን ነው ገዥዎች የገለጹት፡፡
አሚኮ በባሕርዳር ከተማ የትንሣዔ በዓልን መሰረት በማድረግ የእርድ እንስሳት ግብይትን ተመልክቷል፡፡ ሻጭና ገዥንም አነጋግሯል፡፡ ግብይት ሲፈጽሙ ያገኘናቸው ገዥዎች እንዳሉት የእርድ እንስሳት አቅርቦት ቢኖርም በእንስሳት የተጋነነ ዋጋ ጥሪ ምክንያት የፈለጉትን ለመግዛት አልቻሉም፡፡ አሁን ላይ ያለው የእርድ እንስሳት ዋጋ ከገና በዓል ዋጋ መጨመሩን ነው የገለጹልን፡፡
በግብይቱ እንደቁም እንስሳቱ መጠን ቢለያይም ከፍተኛው የዋጋ ጥሪ
👉 በግና ፍየል ከ5 ሺህ እስከ 17 ሺህ ብር
👉ከብት ከ35 ሺህ እስከ 130 ሺህ ብር
👉ዶሮ ከ600 እስከ 900 ብር እንደኾነ ገዥዎች ነግረውናል፡፡
የእርድ እንስሳት አቅራቢዎች እንዳሉት ደግሞ በከተማ አሥተዳደሩ የእርድ እንስሳት አቅርቦት ቢኖርም የማኅበረሰቡ የመግዛት ፍላጎት ዝቅተኛ ነው፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!