
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 28/2012 ዓ.ም (አብመድ) በውይይቱ የመንግሥትን የሕግ አስከባሪነት ብቻ ሳይሆን የሕግ አክባሪነትም ለማጠናከር የተዘጋጀ መሆኑን የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ ተናግረዋል፡፡
ክልላዊና ሀገራዊ ሠላምን ለማረጋገጥ የሕግ የበላይነት መከበር እንዳለበት ያመላከቱት ወይዘሮ ወርቅሰሙ ውይይቱ ጥሩ ግብዓት እንደሚገኝት ያላቸውን ተስፋም ገልጸዋል፡፡
ወይይቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመሥገን ጥሩነህ እየመሩት፤ የውይይት መነሻ ጽሑፍ ደግሞ በአቶ ገረመው ገብረጻድቅ እየቀረበ ነው፡፡
ዘጋቢ፡- አብርሃም በዕውቀት