የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ ሊቃነጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት የፀሎተ ሐሙስ በዓል እየተከበረ ነው፡፡

88
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የፀሎተ ሐሙስ በዓል በአዲስ አበባ በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ በተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ በዛሬዋ እለት ዝቅ ብሎ የሐዋርያቱን እግር በማጠብ ፍጹም ትህትናን እና ታዛዥነትን ማስተማሩን በማሰብ ነው በዓሉ እየተከበረ የሚገኘው፡፡
በዓሉ በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እንዲሁም በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
በዚህም የእግር አጠባ ሥነ-ሥርዓትን ታላላቅ አባቶች የምዕመናንን እግር በማጠብ የኢየሱስ ክርስቶስን አርዓያነት ተከትለው ሥርዓቱን ይፈጽማሉ።
በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍጹም ትህትናን ያስተማረበትና ዝቅ ብሎ የደቀመዛሙርቱን እግር ያጠበበት በመሆኑ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል።
በዓሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ ሊቃነጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በአዲስ አበባ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተክርስትያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረም ነው፡፡ ይህ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ትህትና የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት ፣ከደቀመዛሙርቶቹ ጋር የመጨረሻዋን እራት ያከናወነባትና የክርስትና የሕይወት ማሕተም የኾነውን ምስጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለትም ነው።
ዘጋቢ፡- ሳሙኤል ኪሮስ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ሰሙነ ሕማማት” – የሕማማት ሳምንት
Next article“ማንኛውንም ጥያቄ በውይይት ብቻ መፍታት ተገቢ ነው” የሰሜን ምሥራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ብርሃኑ ጥላሁን