በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረውን እሳት መቆጣጠር መቻሉን የፓርኩ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

79
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረውን እሳት መቆጣጠር እንደተቻለ የፓርኩ ጽሕፈት ቤት ኅላፊ አዛናው ከፍያለው ገልጸዋል። ቃጠሎው ባለፈው መጋቢት 29/2015 ዓ.ም ከሰዓት የተከሰተ ሲኾን የአካባቢው ማኅበረሰብ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ መቆጣጠር ተችሏል።
የእሳት አደጋው የተነሳው በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ግጭ እና እሜት ጎጎ በተባሉ አካባቢዎች ነው። አቶ አዛናው በውል ባልተለየ ምክንያት የተነሳውን እሳት በተደረገው የተቀናጀ ርብርብ መቆጣጠር ቢቻልም አሁንም ድረስ የሚጨስ እና ዳግም ሊያገረሽ የሚችል የእሳት ቅሪት ስለመኖሩ ተናግረዋል። የፓርኩ ጠባቂዎች የሚጨሰውን ክፍል በመከታተል እያጠፉ እንደሚገኙም አቶ አዛናው ገልጸዋል።
የአካባቢው ማኅበረሰብ፣ ስካውቶች እና ሁሉም የጥበቃ አካላት የእሳት አደጋው በቀጣይም እንዳይከሰት በንቃት እንደሚከታተሉም የፓርኩ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተናግረዋ።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበኩር ጋዜጣ ሚያዝያ 02/2015 ዓ.ም ዕትም
Next article“የልዩ ኀይል ሪፎርም የሚካሄደው የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የሚያረጋግጥ፣ የሀገርን አንድነት የሚያጸና ጠንካራ የጸጥታ ኀይል ለመገንባት ነው” አቶ ግርማ የሺጥላ